Amos 4

እስራኤል ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም

1እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤
ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣
ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን”
የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤
2ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሏል፤
“እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበት
ትሩፋናችሁ እንኳ፣ በዓሣ መንጠቆ
የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል።
3እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያ
ወደ ሬማንም
በተለያዩ የዕብራይስጥ ቃላት የተከፈለው የመጀመሪያው የዕብራይስጥ ቅጅ (የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ይመ) የጭቈና ተራራ ሆይ ራቅ ይላል።
ትጣላላችሁ፤”
ይላል እግዚአብሔር
4“ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤
ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤
በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣
በየሦስቱ
በየሦስቱ ቀናት ዐሥራታችሁን የሚሉ አሉ።
ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።
5እርሾ ያለበትን እንጀራ የምስጋና
መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤
በፈቃዳችሁም በምታቀርቡት ቍርባን ተመኩ፤
እናንት እስራኤላውያን በእነርሱም ተኵራሩ፤ ማድረግ የምትወድዱት ይህን ነውና፤”
ይላል ጌታ እግዚአብሔር

6“በየከተማው ሆዳችሁን
ዕብራይስጡ ጥርሳችሁን አጠራለሁ ይላል።
ባዶ አደረግሁት፤
በየመንደሩም የምትበሉትን
አሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”
ይላል እግዚአብሔር

7“መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣
ዝናብ ከለከልኋችሁ፤
በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤
በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ
አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣
ሌላው ዝናብ ዐጥቶ ደረቀ።
8ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣
ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤
እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”
ይላል እግዚአብሔር

9“የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤
በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤
አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤
እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”
ይላል እግዚአብሔር

10“በግብፅ ላይ እንዳደረግሁት፣
መቅሠፍትን ላክሁባችሁ፤
ከተማረኩት ፈረሶቻችሁ ጋር፣
ጕልማሶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤
የሰፈራችሁ ግማት አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግሁ፤
እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”
ይላል እግዚአብሔር
11“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣
አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤
ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤
እናንተ ግን ወደ እኔ
ዕብራይስጡ አምላክ ይላል።
አልተመለሳችሁም፤”
ይላል እግዚአብሔር

12“ስለዚህ እስራኤል ሆይ፤ እንደዚህ አደርግብሃለሁ፤
እንደዚህም ስለማደርግብህ፣ እስራኤል ሆይ፤
አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።”

13ተራሮችን የሚሠራ፣
ነፋስን የሚፈጥር፣
ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣
ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣
የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣
ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
Copyright information for AmhNASV